Thursday, February 28, 2013

የሰንበት ትምህርት ቤታችን መልእክት


ፍኖተ ቅዱሳን

በመጀመሪያ እኛ የሰንበት ተማሪ የሆንን ሁላችን፤ በቅድሚያ ልናውቅ የሚገባን ነገር አለ።  እሱም ሃይማኖታችንን ጠንቅቀን ማወቅ እና ቅዱሳን አባቶቻችን የሄዱበትን የሃይማኖት መንገድ መከተል ነው። ለምሳሌ፤
1) ፍኖት ማለት መንገድ ማለት ነው:: በመጽሐፍ ቅዱስ የሰው ሕይወት በመንገድ ተመስሏል:: በመንገድ ላይ ሳለህ በጠላትህ እወቅበት ማለቱ በዚህ ዓለም ሕይወትህ በጠላት ዲያብሎስ ላይ ጠቢብ ሁንበት ማለት ነው:: ማቴ 5;25:: የሰው ሕይወት በመንገድ የተመሰለው በመንገድ ላይ አንዱ ሲወጣበት ሌላው አንዱ ሲወርድበት ሁሉም ወደ አሰበው ሲደርስበት እንደሚኖር ሁሉ በዚህ ዓለም ሕይወትም አንዱ ጽድቅ ሠርቶ ከክብር ወደ ክብር ሲሸጋገርበት ሌላው ደግሞ በሚያልፍ ዘመኑ ፍዳው የማያልፍ ኃጢአት ሲሠራ ኖሮ በወደደው ኃጢአት እንደ ጠፍ ጨረቃ ከክብር እያነሰ ስለሚሄድበት ነው:: ቅዱሳን መንገድ በተባለ በዚህ ዓለም ሕይወታቸው በጠላታቸው በዲያብሎስ ላይ አውቀውበት እርሱን ጠቅጥቀው አልፈው ለክብር የበቁ ሲሆን ይህ ብሎግም ይህንኑ የቅዱሳን ጥበብና ተጋድሎ በአጠቃላይም