Wednesday, March 27, 2013

መፃጉዕ


አትምኢሜይል
  source:- MAHIBERE KIDUSAN                                                                                                                                                                                                        በእመቤት ፈለገ
ልጆች በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት የዓብይ ጾም አረተኛ እሑድ መጻጉዕ
 ይባላል፡፡ ታሪኩም እንደዚህ ነው፡፡ በኢየሩሳሌም በር አጠገብ ቤተሳይዳ የምትባል የመጠመቂያ ቦታ ነበረች በዚያም
ማየት የተሳናቸው፣ መራመድ የማይችሉ ብዙ በሽተኞች በመጠመቂያው ቦታ ተኝተው የውሃውን መናወጥ ይጠባበቁ ነበር፡፡
 ለምን መሰላችሁ ልጆች የእግዚአብሔር መልአክ ወደ መጠመቂያው ወርዶ ውኃውን በሚያናውጠው ጊዜ÷ ከውኃው መናወጥ
 በኋላ በመጀመሪያ ወርዶ የሚጠመቅ ካለበት ደዌ ሁሉ ይፈወስ /ይድን/ ነበር፡፡ በዚያ ቦታም ከታመመ ሰላሳ ስምንት
ዓመት የሆነው አንድ ሰው ነበር፡፡ ስሙም መጻጉዕ ይባላል፡፡ ልጆች መጻጉዕ እንዴት በሕመም እንደተሰቃየ አያችሁ?


ታዲያ ልጆች ጌታችን ኢየሱስ ያሰው በአልጋው ተኝቶ ባየ ጊዜ በበሽታ ብዙ ዘመን እንደቆየ አውቆ “ልትድን ትወዳለህን?” አለው፡፡
 መጻጉዕም “አዎን ጌታዬ ሆይ ነገር ግን ውኃው በተናወጠ ጊዜ ወደ መጠመቂያው የሚያወርደኝ ሰው የለኝም፤ እኔ በምመጣበት
 ጊዜ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል” አለው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም “ተነስና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” አለው፡፡ ወዲያውኑ ያሰው
 ድኖ አልጋውን ተሸክሞ ሄደ፡፡ ልጆች ታሪኩን በደንብ አነበባችሁ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጻጉዕን ከበሽታው እንደፈወሰው አነበባችሁ አይደል?
 ጎበዞች! እኛም በታመምን ጊዜ እንደመጻዕጉም የሚረዳን ሰው ባጣን ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችን ይረዳናል፡፡
ደህና ሰንብቱ!

Monday, March 25, 2013

የሰንበት ትምህርት ቤት አመሰራረት ታሪክ (በዲያቆን ዳንኤል ክብረት)



“የክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር” ብፁእ አቡነ ሺኖዳ 3ኛ


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቃየ ፤ ነገር ግን ስለእኛ ተሰቃየ ፡ ስለእኛ ተሰቃየ ፤ እኛን ከስቃይ ከህማም ያድነን ዘንድ እርሱ ተሰቃየ ፡ እኛን ከሞት ያድነን ዘንድ ሞተ ፤ እኛን ከድካም ያሳርፍ ዘንድ እርሱ በእጅጉ ደከመ ፤ ክርስቶስ እኛን ያድነን ዘንድ ተሰቃየ ፡  ስለሌሎች ተሰቃየ ፤ ህማሙ በነፍሱና በስጋው ላይ ወደቀ ፡ ለረጅም ሰአት መስቀሉን ተሽክሞ ነበርና ፡ በሚወድቅ ሰአት ከባዱ መስቀል ተጭኖት ነበርና ፡ የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፍተው እንዲንገላታ አድርገውት ነበርና ፡ ቅዱስ ስጋውን በሚስማር ቸንክረው እንዲሰቃይ አድርገውት  ነበርና ፡  በመስቀል ላይ ለረጅም ሰአት ተሰቅሎ ነበርና ፡ ደሙ እንደውሃ ፈሶ ነበርና ፡ ተደብድቦ ተገርፎም ነበርና ፤ ደበደቡት ፡ ገረፉት ፡ ተፉበት እኒህ ሁሉ የጌታችን የስጋ ህማሙ ናቸው ፤ ነገር ግን የተቀበለው መከራ ይህ ብቻ አይደለም ፤  የስጋ ህማም ያልሆነ የነፍስ ህማምንም ታግሷል እንጂ ፤   እንደ ርጉም እንደበደለኛ መቆጠሩ ይህ አንዱ ህማሙ ነበር ፡ የመሰደቡ ህማም ይህ አንዱ ህማሙ ነበር ፡ በሁሉ ፊት መዋረዱ ይህ አንዱ ህማሙ ነበር ፡ የመካድ ህማም ፡ በሁሉ የመወገዝ ህማም ፡ እኒህም ሌላው ህማሙ ናቸው ፤ ሃዋርያቱ እንኳን ሳይቀሩ ትተውት ሽሹ ፡  ጴጥሮስ እንኳን ሶስት ጊዜ ካደው ፡ በወንድሞች መካከል በድካም መታየት ይህ ራሱ ለነፍስ ትልቅ ህማሟ ነው፡፡

            ጌታችን ግን ይህ ሁሉ መከራ ሲደርስበት ራሱን ይከላከል ዘንድ ምንም አላደረገም ፡ ራሱን አልተከላከለም ፤ በገዥወች የፍርድ ዙፋን ፊት በቆመ ጊዜ የውሽት ምስክሮችንና ክሶችን አቀረቡበት ፡ እርሱ ግን ዝም አለ ፡ ምላሽም አላቀረበም ፡ “አንተ ስለራስህ አትናገርምን? እኒህ ሁሉ ባንተ ላይ ሲመሰክሩ እንደምን ዝም ትላለህ?” እስኪሉት ድረስ ዝም አለ ፡  በጲላጦስም ፊት ሁሉ በሃሰት ሲከሱት ምንም አልተናገረም  ፡ ዝም አለ እንጂ ፤ ራሱን ይከላከል ዘንድ አንዳች አላደረገም ፤ ራሱንስ ይከላከል ዘንድ ቢወድ ይህ በእርሱ ዘንድ እጅግ ቀላል ነበረ ፡ በክርስቶስ ዘንድ ያለ እውቀት ፡ ማመዛዘን ፡ መረዳትና ማሳመኛ ሊከላከልለት በቂ ነበርና ፤ ነገር ግን ፈቃዱ ራሱን ይከላከል ዘንድ አልነበረም ፡ ፈቃዱ ሌሎች ያድን ዘንድ ነበር እንጂ ፤ ሌሎቹም ይድኑ ዘንድ እርሱ መሰቀል ነበረበት ፤ ታገሉት “ አንተ የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ ራስህን ከመስቀል ላይ አውርድ” እያሉ ታገሉት ፤ እርሱ ከመስቀል ወርዶስ ቢሆን እኛ ሁላችን በጠፋን ነበር ፤ እርሱ ግን እኛ እንድንለት ዘንድ ስለእኛ በእነሱ መሽነፍን ወደደ ፡ ስላቃቸውን ይታገስ ዘንድ መረጠ ፤ እራሱንስ ይከላከል ዘንድ አልወደደም ስለሁሉ ሰው መከላከልን መርጧልና ፡ እኛን ያድን ዘንድ ስለሁሉ እርሱ ዋስ ሆነ ፤
ዳግምም ጌታችን ራሱ ስለራሱ ፈቃድ ተሰቃየ ፤ ራሱ ? እንደምን  በራሱ ፈቃድ ተሰቃየ? ምን ማለት ነው? ይህ ማለት ክርስቶስ ራሱ አይሁድ ሊይዙት ወደሚፈልጉበት ቦታ በእግሩ ሄዷልና ነው ፡ የት ቦታ አይሁድ ሊይዙት እንደተማከሩ እርሱ አስቀድሞ ያውቅ ነበርና ፡ ጊዜውንም ያውቅ ነበርና ፡ ስለዚህም እርሱ ራሱ ወደሚይዙበት ቦታ ሄደ ፡ ይሁዳ አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት ራሱን አሳልፎ ሰጠ ፡ ዳግምም በራሱ ፈቃድ ራሱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ ፡ ስለዚህም እንደዚህ አለ ፦ “ነፍሴን ላጠፋትም ላነሳትም ስልጣን አለኝ” በዚህም ከሚደርስበት ስቃይ ሁሉ ራሱን ይጠብቅ ዘንድ ይችል ነበር ፡ ነገር ግን በጄ አላለም ፤ እርሱ በራሱ ፈቃድ ለእኛ ራሱን መስዋእት አደረገ፡፡

            በጌታችን በክርስቶስ ያየነው ስቃይ ሁሉ ጌታችን ለእኛ ያለው የፍቅር ምልክቶች ናቸው ፤  ጌታችን “ስለወዳጆቹ ነፍሱን ከሚሰጥ የሚበልጥ ፍቅር የለም” አለን ፡ ስለዚህም እነዚያ ስቃዮቹ ሁሉ ስቃዮች ብቻ አልነበሩም ፍቅሩም ነበሩ እንጂ

Friday, March 22, 2013

፫ኛ ሳምንት ምኩራብ

ምንጭ፦ አትሮንስ-የዲያቆን ኤርምያስ ነቢዩ ገጽ (www.ermiasnebiyu.org)

የአብይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት /ምኩራብ/


    በዚህ በሦስተኛው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦

በግዕዝ፦

እስመ ቅንዓተ ቤተከ በልዓኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትኤየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ

በአማርኛ፦ 

የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥ ለስድብም ሆነብኝ። መዝ.፷፰፡፱

በዚህ የሦስተኛ የአብይ ጾም ሳምንት አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ የወንጌልን ትምህርት እንዳስተማረ፤ ብዙ ድውያንን
እንደፈወሰ፤ የሰንበት ጌታ እንደሆነ፤ የአባቴ ቤት የጸሎት ቤት እንጂ የንግድ ቦታአይደለም በማለት በቤተ መቅደሱ አካባቢ የሚነግዱ ነጋዴዎችን ስለ መገሰጹ ትምህርትይሰጥበታል። በተለይም በነብዩ በኢሳይያስ እንደተጻፈ ጌታ በአይሁድ ምኩራብ ገብቶመጽሐፍ እንዲሰጡት ጠይቆ የሚሰሙት ቃል ዛሬ በጆሯቸው እንደተፈጸመ እንዲህ ሲልእንደነገራቸው ይዘከርበታል፦
ኢየሱስም በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለችው
አገር ሁሉ ዝና ወጣ። እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር፥ ሁሉም ያመሰግኑት ነበር።
ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥

ሊያነብም ተነሣ። የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ
ጊዜ። የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤
ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ
ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ
አገኘ። መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት
ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። እርሱም። ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ
ተፈጸመ ይላቸው ጀመር። ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር ከአፉም ከሚወጣው ከጸጋው
ቃል የተነሣ እየተደነቁ። ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምንይሉ ነበር። እርሱም። ያለ
ጥርጥር ይህን ምሳሌ። ባለ መድኃኒት ሆይ፥ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም
እንዳደረግኸው የሰማነውን ሁሉ በዚህ በገዛ አገርህ ደግሞ አድርግ ትሉኛላችሁ
አላቸው። ሉቃ.፬፡፲፬-፳፫
ጌታችን በምድር ሲመላለስ ከዚህ ቀደም በምኩራቦቻቸው ተሰምቶ
የማይታወቅ የወንጌል ትምህርት እንዳስተማራቸውና ዕውራን እንዲያዩ፤ ደንቆሮዎች
እንዲሰሙ፤ ዲዳዎች እንዲናገሩ በማድረግ እንዲሁም ደግሞ ሙታንን በማሥነሳትየተለያዩ ድንቅ ተኣምራቶችን በማድረግ የወንጌልን ኃይል ስለማሳየቱ ይተረክበታል።የቤትህ ቅናት በላኝ ተብሎ እንደተጻፈ ሕገ እግዚአብሔር እንዲፈጸም፤ ሕገ ቤተ ክርስቲያንእንዳይፈርስ፤ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዳይበላሽ በአይሁድ ምኩራብ በመግባትእንዳስተማረ ሁሉ ዛሬም እያንዳንዳችን የቤተ ክርስቲያንን ነገር ለቤተ ክርስቲያን በማድረግበቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ነገርን ብቻ በመሥራት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርንበመከተል ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ እንደሚገባን ሰፊ ትምህርት ይሰጥበታል። ቤተክርስቲያን የጌታ ሥጋ እና ደም የሚፈተትባት፤ ሰዎች ዘላለማዊ ሕይወትን የሚያገኙባትመሆኗም ይነገርባታል። ጌታችን በቅፍርናሆም ምኩራብ የሕይወት እንጀራ እርሱ እንደመሆኑ ያስተማረበት አብይ ክፍል በዚህ በሦስተኛው ሳምንት የአብይ ጾም በሰፊውይነገራል። አይሁድ የእውነትን ቃል ሰምተው አንገታቸውን እንዳደነደኑ፤ ሥጋዬን የበላደሜን የጠጣ የዘላላም ሕይወት አለው በሚለው የጌታ ትምህርት እንዴት ሊሆን ይችላልበማለት ማጉረምረማቸው በዚሁ ክፍል አብሮ ተጠቃሽ ነው። ጌታም እስራኤል በምድረበዳ በልተውት የነበሩት መና እና እውነተኛው የሕይወት እንጀራ ያላቸውን ልዩነትበማነፃፀር እንዲህ ሲል
አስተምሯቸዋል፦
አብን ያየ ማንም የለም፤ ከእግዚአብሔር ከሆነ በቀር፥ እርሱ አብን አይቶአል።
እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው። የሕይወት

Wednesday, March 20, 2013

«...ለእግዚአብሔር ተገዛ...»

v  ለ እግዚአብሔር ተገዛ
v  እንዲህ የሆንክ እንደሆነ መከራ በመጣብህ ጊዜ ሲረዳህ ታገኘዋለህ። ልመናህንም ይሰማሃል።
v  ኃጢአት ከመስራት አስቀድሞ አንድም ኃጢአት ሰርተህ በመከራ ከመሰናከል አስቀድሞ ለምን ማልድ።
v  መከራ መጥቶብህ መከራውን ለማራቅ ከምትጸልየው ጸሎት አስቀድሞ  ለሚገባ ንሰሐ ተዘጋጅ።
v  ክፉ ሰው እና ከክፉ ግብሩ ተለይ።
v  ወደኔ ተመለሱ ይቅር እላችኋለሁ።  በፍጹም ልባችሁ ወደኔ ተመለሱ ይልሃል እግዚአብሔር
v  በህይወት ትኖሩ ዘንድ ታዘዙልኝ፡፡
v  እግዚአብሔርን በጸሎት ጥራው። ያድነኛል ብለህ በጸሎት ብትጠራው ልመናህን ይሰማሃል ያደርግልሃል።

Monday, March 18, 2013

የአብይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት (ቅድስት)

ምንጭ፦ የዲያቆን ኤርምያስ ነቢዩ ገጽ (www.ermiasnebiyu.org)


በዚህ በመጀመርያው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦

በግዕዝ፦ 

እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ
አሚን ወሰናይት ቅድሜሁ
ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ

በአማርኛ፦ 

እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
ምስጋናና ውበት በፊቱ ነው፥
ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው። (መዝ.፺፭(፺፮)፡፭


በዚህ የሁለተኛ የአብይ ጾም ሳምንት ስለ እግዚአብሔር ቅድስና ቤተ
ክርስቲያን ልጆቿን ታስተምራለች። እግዚአብሔር ቅዱስ በመሆኑ የተቀደሰ ነገርያስፈልገዋልና ሰው ሁሉ በቅድስና መንገድ በመመላለስ የክብሩ ባለቤት የመንግሥቱ ወራሽእንዲሆን እግዚአብሔር እኔ ቅዱሳን ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ በማለት ስለማስተማሩ ሰፊትምህርት ይሰጥበታል። ሰውም፤ መላእክትም፤ ቦታም፤ ዕለትም
ለእግዚአብሔር በእግዚአብሔር ተቀድሰዋል። ቅዱሳን መላእክትና ቅዱሳን ሰዎችየእግዚአብሔርን ቅድስና ተረድተው እግዚአብሔርን በማመስገን ሲተጉ ቅዱሳት ቦታዎችእና ዕለታት የቅዱሳኑ ነገር ሲታሰብባቸው፤ ጸሎት ሲደርስባቸው እና ለእግዚአብሔር እናእግዚአብሔር ለቀደሳቸው ቅዱሳን ስም መጠሪያ ሆነው ሲያገለግሉ ይኖራሉ።እግዚአብሔርን ማየት እና የእግዚአብሔር የሆነን ሥርዓት መከተል ስለሚያስችል ዕለትዕለት መልካም በማድረግ ቤተ መቅደስ ተብሎ የተነገረለትን ሰውነታችንን በመጠበቅለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕቃ ሆነን መቅረብ እንደሚገባ
ይዘከርበታል። እግዚአብሔር አምላካችን ቅዱስ ነው እያልን በልባችን አምነን በአፋችን
መስክረን በተግባር ግን ከቅድስና ርቀን እንዳንኖር እግዚአብሔር እንደቀደሰን እናልጅነትን እንደሰጠን በማመን በተቀደሰ ሁኔታ መኖር ይገባናል። የእግዚአብሔርን ቅድስናእንዲሁም ደግሞ እግዚአብሔር ለሰዎች ቅድስናን እንደሚሰጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልየተለያዩ ክፍሎች እንዲህ በማለት ይገልጸዋል፦

እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ
መቅደሱን ሞልቶት ነበር። ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም
ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን
ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር። አንዱም ለአንዱ። ቅዱስ፥ ቅዱስ፥
ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ
ይጮኽ ነበር። የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፥ ቤቱንም
ጢስ ሞላበት። ኢሳ.፮፡፩-

በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ
ወደ ዓለም ላክኋቸው፤ እነርሱም ደግሞ በእውነት የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ
እነርሱ እቀድሳለሁ። ዮሐ.፲፯፡፲፯-፲፱

ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ
ሆይ፥ መንገድህ ጻድቅና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ፥ የማይፈራህና ስምህን
የማያከብር ማን ነውአንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፥ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ
አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ በፊትህም ይሰግዳሉ እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን
ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ። ራእ.፭፡፫-

በዚህ በሁለተኛው ሳምንት በቅዳሴ ላይ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሙሉውምንባብ
ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፦

እንግዲህ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ
ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ፥ እናንተ ደግሞ

ጾም ለምን?(ክፍል አንድ)


ጾም ለምን?(ክፍል አንድ)
      የጾም ጥቅሙና አገልግሎቱ በጥንት አበዉ ጀምሮ በጎላ በተረዳ ነገር የታወቀ ነዉ፡፡ሆኖም በዘመናችን ብዙ ሰዎች ስለምን እንደሚጾሙ ጠንቅቀዉ ካለመረዳታቸዉ ይመስላል ጾም ከ እህል ከዉሀ ተከልክሎ ለተወሰኑ ሰዓታት መቆየት ከጥሉላት መባልዕት ብቻ መለየት እንደሆነ ያስባሉ፡፡‹‹ጾም አከሳኝ››በማለት ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡የጾም ዓላማ ይህ ይመስላቸዋል፡፡እንዲህ ግን አይደለም፡፡ሰዉ ለስርየተ አበሳ ዋጋዉ እንዲበዛለት፤የፈቲዉ ጾር ያደክም ዘንድ፤ስጋ ለነባቢት ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ ይጾማልና፡፡ስለሆነም የጾምን ጥቅም እንደሚከተለዉ በዝርዝር እናቀርባለን፡፡
ጾም ፈቃደ ስጋን ለነባቢት ነፍስ ለማስገዛት ይጠቅማል
ፈቃደ ስጋና ፈቃደ ነፍስ ሁልጊዜ እርስ በ እርሳቸዉ ይቀዋወማሉ፡፡አንዱ በአንዱ ላይ የበላይ በመሆን ፈቃዱን ሊያሰራዉ ያሻል፡፡ቅዱስ ጳዉሎስ‹‹በፈቃደ ነፍስ ጸንታችሁ ኑሩ ፈቃደ ስጋችሁን ግን አትስሩ ፡፡ስጋ ነፍስ ልትሰራዉ የማትወደዉን ይወዳልና ነፍስም ስጋ ሊሰራዉ የማይወደዉን ትወዳለችና እርስ በእርሳቸዉም ይጣላሉ ፡፡››በማለት ተናግሯል፡፡ገላ 5-16፡፡ስለሆነም ፈቃደ ስጋ በፈቃደ ነፍስ ላይ ኃይል እንዳይኖረዉ መጾም ፤መጸለይ፤መመጽወት ያስፈልጋል፡፡ሰዉ ፈቃዳተ ነፍሱን በመፈጸሙ ከፈጣሪ ከአምላኩ ጋር ህብረት አንድነት ይኖረዋል፡፡ከፈተናና ከመከራ ይድናል፡፡የፈለገዉንም ያገኛል ፡፡ለፈቃደ ስጋዉ ከ ተገዛ ግን ራሱን የኃጢያት ባሪያ ያደርገዋል ሮሜ 7-10
ጾም እግዚአብሔርን ለመለመንና ከእርሱ መልካም የሆነዉን ነገር ለመቀበል ይጠቅማል
     መጾም ከእግዚአብሔር የሚገኘዉን ጸጋና በረከት ይቅርታን ምህረትን ለማጎናጸፍ ይጠቅማል፡፡ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል ፡መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና የሚፈልግም ያገኛል››ብሏል፡፡ማቴ 7-7 የቀደምት አበዉን ሕይወት ስንመለከት ጾመዉ ያፈሩበት ጊዜ እንዳልነበር እንረዳለን ፡፡ለአብነት የሚከተሉትን እናያለን፡፡
    Ω ሊቀ ነቢያት ሙሴ
በደብረ ሲና 40 ማዓልት እና ሌሊት ከጾመ በኋላ በግብር አምላካዊ የተጻፉ ዐስርቱ ቃላትን፤ሕገ ኦሪትን፤ታቦተ ጽዮንን ተቀብሏል፡፡
     Ω ቆርነሌዎስ
ቆርነሌዎስ የፍልስጤም ክፍል በምትሆን በቂሳርያ መቶ አለቃ ሆኖ ተሾመ ከዋክብት ሲያመልክ የነበረ ሰዉ ነዉ፡፡በኋላም የሐዋርያትን የጃቸዉን ተአምራት፤የስብከታቸዉን ዜና ሰምቶ ወዲያዉኑ ለ አማልክት መስገድን ተወ ከዚህም በኋላ የሚጸልይ፤የሚጾም፤ለችግረኞች የሚመጸዉት ሆነ፡፡ቸር ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ይቅር ብሎት በ ሐዋርያዉ ቅ/ጴጥሮስ አማካይነት ቆርነሌወስ እስከ ቤተሰቦቹ ፤እንደዚሁም በአካባቢዉ ከ ነበሩት ብዝዎቹ አምነዉ ተጠምቀዋል፡፡የሐዋ 10-1 እነ ነቢዩ ዳንኤል በምርኮ እያሉ የባቢሎን ቤተ መንግስት ጮማና ጠጅ ሳያጓጓቸዉ ጥራጥሬና ዉሃ ብቻ እየተመገቡ አስር ቀናት ጾሙ፡፡ከንጉሱ ገበታ ከተመገቡት ብላቴኖች ሁሉ ይልቅ ፊታቸዉ አምሮና ስጋቸዉ ወፍሮ ታየ ፡፡ስጋ ባለመባላታቸዉ አልከሱም አልጠቆሩም ፡፡እግዚአብሔር  ለእነዚህ ባላቴኖች በትምህርትና በጥበብ ሁሉ ማስተዋልን ሰጣቸዉ ፡፡ዳን 1-8 -1
   Ω ቅዱሳን ሐዋርያት
የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ሐዋርያት ጾመዉ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እንደተቀበሉ ቅዱስ ሉቃስ ጽፎልናል፡፡የሐዋ 13-1፡፤ቅ/ጳዉሎስም አብዛኛዉን ጊዜ በጾም ያሳልፍ የነበረዉ መልካም ነገርን ከእግዚአብሔርን ለመቀበል ነዉ፡፡
ጾም ኀዘንን ለመግለጽ ይጠቅማል
ጾም ስለራሳችን እና ስለሌሎች(ስለተሰደዱ፤ ስለታሰሩ፤ስለተጨነቁ፤በጦርነት ስለሚሰቃዩ፤በደዌ ዳኛና በአልጋ ቁራኛ ስለተያዙ ወገኖች)ለማዘንና ከእግዚአብሔር ምህረትን ለመለመን ይጠቅማል፡፤የቀደሙትን አባቶች አነዋወር ስንመለከት ኀዘን መከራ ባገኛቸዉ ጊዜ ሁሉ ማሶገጃ መፍትሔ አድርገዉ የሚወስዱት ጾምና ጸሎትን ነበር፡፡ለአብነት የሚከተሉትን አንመልከት፡፡
         ûከክርስቶስ ልደት 400 ዓመት በፊት ይኖር የነበረ ነህምያ የወገኖቹን ዉርደትና መከራ የኢየሩሳሌም የቅጥሮቿ መፍረስ የበሮቿ መቃጠል በሰማ ጊዜ ኀዘኑን የገለጠዉ በጾምና በጸሎት ነበር፡፡
          ûዕዝራም በምርኮ ስለነበሩት ወገኖቹ ኃጢአትና በደል ባለቀሰ ጊዜ ኀዘኑን የገለጠዉ በጾም ነበር፡፡ዕዝ 10-6
          ûአይሁድ በንጉሱ በ አርጤክስ ዘመን በሐማ ተንኮል የሞት አዋጅ በታወጀባቸዉ ጊዜ ኀዘናቸዉን የገለጡት በጾም ነዉ፡፡ጾምና ጸሎታቸዉ በ እግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አግኝቶ በመርዶክዮስ ፋንታ ሐማ ተሰቀለ አይሁድም ከታወጀባቸዉ የሞት አዋጅ ነጻመዉጣትም ችለዋል፡፡
            ሐዋርያዉ ቅዱስ ያዕቆብ ‹‹እናንተ ኃጢአተኞች እጃችሁን አንሱ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ ልባችሁን አጥሩ ፡፡ተጨነቁ ና እዘኑ አልቅሱም ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወድትካዜ ይለወጥ ››ይላል ፡፡ያዕ 4-8-9 በ ኢዮኤልም እንዲህ ተባሏል‹‹በጽዮን መለከትን ንፉ ጾምን ቀድሱ ጉባኤንም አዉጁ ሕዝብንም አከማችሁ ማኅበሩንም ቀድሱ ጉባኤዉንም አዉጁ ሕዝቡን አከማችቹ ሙሽራዉ ከእልፍኝ ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይዉጡ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ካህናት ከወለሉና ከመሰዊያዉ መካከል እያለቀሱ አቤቱ ለህዝብህ ራራ ይበሉ፡፡››ኢዩ 2-15
          ጾም ድካምን አዉቆ ሰዉነትን ቅድመ እግዚአብሔር ለማዋረድ ዋነኛ መሳሪያ ነዉ
በአገር ላይ ያልታሰበ ፈተና ሲያጋጥም ሕዝብ እንዲጾም እንዲጸልይ በእግዚአብሔር ፊት እራሱን እንዲያዋርድ ጾም ይታወጃል ፡፡ምክነያቱም ጾም ወደ እግዚ አብሔር ልመና የማቅረቢያና የይቅርታ መጠየቂያ መንገድ ስለሆነ ራስን በ እግዚአብሔር ፊት በጾም ማዋረድ ክብር ነዉ፡፡‹‹እንግዲህ በጊዜዉ ከፍ እንዲያደርጓችሁ ከ ኃይለኛዉ ካግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ››እንዲል ቅዱስ ጴጥሮስ 1ኛ ጴጥ 5-6፡፡ራስን ማዋረድ መከራንና ትዕቢትን አርቆ ክብርን ያለብሳል፡፡
ጸም ድካማችን እንድንገነዘብ እኛነታችን እንድናዉቅ ይረዳናል፡፡ድካምንም ማወቅ ለትሩፋት መሰረት መጀመሪያ ናት፡፡ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ግንኙነት የነበራቸዉ አባቶች ሰዉነታቸዉን አዋረዱ፡፡እግዚአብሔርም ልመናቸዉን ሰማቸዉ፡፡የፈለጉትንም ነገር ሰጣቸዉ፡፡ስለዚህም ዕዝራ‹‹በፈጣሪያችን ፊት እናዋርድ ዘንድ ጎዳናችን ያቀናልን ዘንድ ለልጆቻችንናለፍጥረቱም ሁሉ ጎዳናቸዉን ያቀናልን ዘንድ አኀዋ በሚባል ወንዝ ጾምን እንጹም ብየ አዋጅ ነገርኩኝ ስለዚህም ነገር ጾምን ወደ እግዚአብሔር ለመንን እርሱም ተለመነን››አለ  ዕዝ 8-21-23፡፡እንዲሁም ነቢዩ ዳንኤል በጾም ሰዉነቱን በ ፈጣሪዉ ፊት በማዋረዱ ልመናዉ ተሰምቶለታል
 ፡፡ይሄዉም ሊታወቅ መልአኩ በሚስፈራ ግርማ ተገልጦ‹‹ዳንኤል ሆይ አትፍራ ልብህ ያስተዉል ዘንድ ሰዉነትም በ አምላክ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረክበት ከመጀመሪዉ ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቷል እኔም ስለቃልህ መጥቻለሁ››ብሎታል ዳን 10-12

                         ብሒለ  አበዉ
 & ‹‹ብዙ ከመብላትና ብዙ ከመጠጣት የማይከለከል ሰዉ ሰይጣነ ዝሙትን ድል አይነሳዉም፡፡››(ማር ይስሀቅ)
 & ‹‹መመጽወትና መጾም ለነፍስ ህይወትን ለስጋ ጤንነትን ይሰጣል፡፡››(አንጋረ ፈላስፋ)
 & ‹‹ያለ ጸሎት መንፋሰዊ ነኝ የሚል ሰዉ እሳት መካከል ገብቶ የሚጫወትን የ እሳት እራትን ይመስላል፡፡››(ማር ይስሐቅ)
 & ‹‹ልጀ ሆይ አንተ በራስህ ላይ ስትፍረድ እግዚአብሔር ፍርዱን ያነሳልሃል አንተ በራሰህ ላይ ባትፈርድ ግን  እግዚአብሔር  ይፈርድብሀል(ታላቁ መቃሪዮስ)
 & ‹‹በወንድሙ ወድቀት የሚደሰት ሰዉ ተመሳሳይ ወድቀት ይጠብቀዋል››(ቅዱስ ኤፍሬም)
 & ‹‹የወንድምህን ኃጢአት መሸፈንና ያእርሱን ኃጢአት እንደራስህ አድርግህ በእርሱ ፋንታ መሞት ካልቻልክ ቢያንስ ስለ ኃጢአቱ አትፍረድበት››(ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ)
 & ‹‹በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ታገኝ ዘንድ ታገስ››(ማር ይስሐቅ)
                          ስንት ይሆን ኪሎየ
           በሕይወት መስመር ላይ በኑሮ ጎዳና
          ጉዞየ ከሆነ ዉሃ አልባ ደመና
           ዘንግቸ ከወጣሁ የፍቅር እንጎቻ
          ተስተካክሎ ቢቆም ልብስና ስጋየ
           በነፍስ ሚዛን ላይ ስንት ይሆን ኪሎየ
                                  ምንጭ፤-ሐመር 17ኛ ዓመት ቁ 2 ግንቦት -ሰኔ 2001ዓ/ም
        
ወስብሐት ለ እግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር!!

Friday, March 15, 2013

ዜና

ዜና አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት

የደብረ ምሕረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳድር ማረሚያ ቤት የተጠናከረ የወንጌል አገልግሎት መስጠት ጀመረ።  በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ ክርስቲያን ታራሚዎች ከዚህ ቀደም የተጠናከረ መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት አለመቻላቸውን ጠቅሰው ሰንበት ትምህርት ቤቱ በራሳቸው ተነሳሽነት በቅዱስ መጽሐፍ እንደታዘዘው ወንጌል የተራብነውን እኛን እዚህ ድረስ በመምጣት ማገልገሉን ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል።  ሰንበት ትምህርት ቤቱ በማረሚያ ቤቱ በዕለተ እሁድ ለሁለት ሰዓት የሚቆይ ስብከት፤ ያሬዳዊ ዝማሬ እንዲሁም አጽናኝ የሆኑ ስነ ጽሑፎችን የሚያቀርብ ሲሆን በሳምንት አንድ ቀን በሚያካሂደው በዚህ መንፈሳዊ ዝግጅት ተቋዳሽ የሆኑ የህግ ታራሚዎች ይበል የሚያሰኝ የባሕርይ ለውጥ ማምጣታቸውን ለመረዳት ተችሏል።

Thursday, March 14, 2013

ወይ ትዕግስት?


ድምፁን ሰምቼ እበሬ
ብከፍተው ቆሞ መምህሬ
ፍቅር ተርቦ እራቱን
አየሁት ያዘነ ፊቱን
ገረመኝ የትዕግሥቱ ጫፍ
ያቆመው አመታት ደጃፍ
እንዴት እስካሁን ጠብቆ
አልሄደም ከቤቴ ርቆ?
ተነጥፈው የሚሰግዱለት
ዘጠና ዘጠኝ እያሉት
ምን ይገደዋል መድኅኔ?
ልጅ ላልሆንኩለት ለኔ


መንግስተ ሰማያት ቀርባለች እና ንስሐ ግቡ!!!

ዜና


     
ዜና አቡን ቤት ቅ/ገብርኤል ሰ/ት/ቤት


    የደ/ም/አ/ቅ/ገብርኤል ሰ/ት/ቤት ‹‹ትውልዱን ወደ ሰ/ት/ቤት ማቅረብ ››በሚል መሪ ቃል በዓይነቱ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ መርሐ ግብር የየካቲት 16/06/05እና17/06/05ዓ/ም ለ2 ተከታታይ ቀናት አካሔደ ፡፡በዕለቱም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ተጋብዘው ከጉባኤው ዓላማ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስብከቶችን የሰጡ ሲሆን የተለያዩ ያሬዳዊ ዜማዎች፤ጭውውቶች ፤መነባንቦችም ቀርበዋል ፡፡በጉባኤውም እጅግ በርካታ ምዕመናን በመገኘት የመንፈሳዊ ግብዣ ተቋዳሽ ከመሆናቸውም በተጨማሪ በሰ/ት/ቤቱ አባል ሆኖ በመታቀፍ የሚጠበቅባቸውን ክርስቲያናዊ ግዴታ ለመወጣትም ቃል ገብተዋል፡፡ የአቡን ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት በሰንበት ት/ቤቱ አባል ሁነው ለማገልገል ቃል ለገቡት የጉባኤው ታደሚዎች በሌላኛው ቀን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐ ግብር በማዘጋጀት ሰንበት ት/ቤት ለነገይቷ ቤተክርስቲያን ህልውና ወሳኝና እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ በሰንበት ት/ቤቱ አባልና አገልጋይ ሆኖ ለመቀጠልም መንፈሳዊ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ በስፋት ተብራርቶላቸዋል ፡፡በእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐ ግብሩ የእግር አጠባ ፤የተለያዩ ትምህርታዊ ስነ ጽሑፎችና ያሬዳዊ ዜማዎችም ቀርበው እንደነበር ለማውቅ ተችሏል ፡፡፤

     በጎንደር ከተማ የሚገኙ የተለያዩ አብያተ ክርስትያናት ዲያቆናት አገልጋዮች በሐዋርያዉ ፊሊጶስ ስም የጽዋ ማህበር በቅርቡ መሰረቱ ፡፡የጽዋ ማህበሩ በዋነኝነት መመስረት ያስፈለገበት ምክንያት ዲያቆናት እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ ፤በጎ ልምዳቸዉን እንዲለዋወጡ፤በቤ/ ክ  ዙሪያ በይበልጥም ከዲቁና ተግባር ጋር ተያይዞ  ስለሚፈጸሙ አገልግሎቶች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ብሎም ከምንፍቅና ተግባር ተቆጥበው ቤተ ክርስቲያናቸዉን ከቀሳጥያን በትጋት እንዲጠጠብቁ፤ነገም ለቅስናና ለምንኩስና በመብቃት በትህትና ቅ/ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ፤ ለማድረግ ታስቦ ነዉ፡፡ይህ የማህበሩ ዓላማ ለዲያቆናቱ በደንብ ተብራረቶ የተገለጸ ሲሆን የመንበረ መንግስት መድኃኔዓም አስተዳዳሪ እና የአራቱ ጉባኤ ምስክር የሆኑት ሊቀ ሊቃዉንት ዕዝራ ሐዲስ በዲያቆናቱ የጽዋ ማህበር በመገኝት ስለ ሚስጥረ ክህነትና በጎ አገልግሎቱ በስፋት አስተምረዋል፡፡አያይዘዉም‹‹ዲያቆናት በብዙ መልኩ ፊት አዉራሪ መሆን ሲገባቸዉ በብዙ መልኩ ተቀዛቅዘዉ››መቆየታቸዉን ጠቅሰዉ ግን እንደዚህ የተደራጀ የጽዋ ማህበር መመስረቱ እንዳስደሰታቸዉ ገልጸዋል፡፡ ይኼ የጽዋ ማህበርም ታይቶ በሚጠፋ ባአሽዋ ላይ የተመሰረተ ቤት እንዳይሆን በጥብቅ አሳስበዋል፡፤ ማኅበረ ፊሊጶስ አባላቱን ለማብዛት ከመቸዉም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ የጽዋ ማህበሩ አስተባባሪዎች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡

 የደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት በሰሜን ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት የተጠናከረ የወንጌል አገልግሎት መስጠት ጀመረ ፡፡በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ ክርስቲያን ታራሚዎች ከዚህ ቀደም የተጠናከረ መንፈሳዊ ት/ት ማግኘት አለመቻላቸውን ጠቅሰው ሰንበት ት/ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት በቅዱስ መጽሐፍ እንደታዘዘው ወንጌል የተራብነውን እኛን እዚህ ድረስ በመምጣት ማገልገሉ ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል ፡፡ሰንበት ት/ቤቱ በማረሚያ ቤቱ  በዕለተ ዕሁድ ለ 2ሰዓት የሚቆይ ሰብከት ፤ያሬዳዊ መዝሙር ፤እንዲሁም አጽናኝ የሆኑ ስነ ጽሑፎች የሚያቀርቡ ሲሆን በሳምንት አንድ ቀን በሚያካሂደው በዚህ መንፈሳዊ ዝግጅት ተቋዳሽ የሚሆኑ የህግ ታራሚዎች ይበል የሚያሰኝ የባህርይ ለውጥ ማምጣት እንደቻሉ ለመረዳት ተችሏል፡፡

Wednesday, March 13, 2013

ደብረ ምሕረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል

የቅዱስ ገብርኤል ሰ/ት/ ቤት መዘምራን  ከሊቃውንቱ ጋር 
በክብረ በዓሉ  
ወረብ 
ሲያቀርቡ


ልጆች እንኳን ለአብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ!!!


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
    ልጆች እንደምን ሰነበታችሁ? ደህና ናችሁ! አሜን የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን፡፡ ልጆች እንደሚታወቀው ቤተክርስትያናችን ከምታዛቸው ሰባት የአዋጅ ወይም የትዕዛዝ አጾዋማት መካከል አንዱና ትልቁ የዐብይን (የሁዳዴ) ፆምን ተቀብለናል፡፡ ልጆች ለምን ዐብይ እነደተባለ ታውቃላችሁ? ዐብይ ማለት ስሙ በራሱ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ታላቅ የተባለበት ምክንያት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም በመሆኑ ነው፡፡
     በዐብይ ጾም 8 ሰንበታት (እሁዶች) አሉ፡፡እነዚህ የየራሳቸው ስያሜዎች አሏቸው፡፡
1. ዘወረደ
2. ቅድስት
3. ምኩራብ
4. መፃጉዕ
5. ደብረዘይት
6. ገብርሄር
7. ኒቆዲሞስ
8. ሆሳዕና ናቸው፡፡
እናንተም ይህን ጾም ለመጾም እድሜአችሁ ሰባት አመት ከደረሰ መጾም ይኖርባችኋል፡፡ውድ ልጆች ጾሙን ስንጾም ታዲያ 
       1 ከሰው ጋር አለመጣላት
       2 አለመሳደብ
       3 ለወላጆች መታዘዝ
       4 ታላቅን ማክበር  እና
       5 አስርቱን ትዕዛዛት በሙሉ ማክበር ይገባል እሺ? ጎበዞች
በሉ ልጆች በሚቀጥለው ዕትም እስክንገናኝ ሰላም ሰንብቱ እሺ፡፡