ግብረ ሰላም ማለት ‹‹ ገብረ ሰላመ››መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ሰላምን አደረገ ፤ተጣልተው የነበሩ ሰማያውያን መላዕክት እና ምድራዊያን ደቂቀ አዳም በመስቀሉ ታረቁ ፤ሰላም ወረደ ማለት ነው፡፡ ይሄውም ‹‹የእግዚአብሔር ሙላቱ በእርሱ እንዲኖር በእርሱ በኩልበመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ያሉት ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዷልና ›› በማለት ቅዱስ ጳውሎስ በቆላ 1፤19-20 ፍንትው አድርጎ ክርስቶስ በመስቀሉ ሰላም እንዳደረገ ገልጾት እናገኛለን፡፡ተድያ ካህናት አባቶች ይህንን ብስራትእና የምስራች ይዘው ከቤተ- እግዚአብሔር ወደ ምዕመናን ቤት‹‹ አዋጅ አዋጅ›› በማለት ይሄዳሉ፡፡ትንሳኤውንም ያበስራሉ፡፡ ይህም ምሰጢር አለው ፡፡ጌታችን እና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ፤ሞቶ፤ወደ መቃብር በወረደብት ጊዜ ሐዋርያት ፍሩኀን ፤ድንጉጻን ነበሩ፡፡በኋላም በ3ኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ በመነሳት ትንሳኤውን በአበሰራቸው ጊዜ ሐሴት አድርገዋል(ዮሐ 20፤20)፡፡በዚህ መሰረት ካህናት የክርስቶስን ትንሳኤ ይዘው ለሐዋርያት ምሳሌ ለሆኑት ለምዕመናን ክርስቶስ ተነስቷል እያሉ ብስራቱን ይናገራሉ፡፡ካህናት ለምዕመናን ‹‹ የክርስቶስ ቸርነቱ ብዛቱ፤40 ፆሙ 50 ብሉ ማለቱ ፤ጾም እንዳትውሉ ፤ዘር እንዳትመትሩ›› በማለት ጊዜው የደስታ፤የሐሴት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ምዕመናንም በክርስቶስ ትንሳኤ ደስ በመሰኘት ቀንዱ የዞረዉን፤ጮማው የሰባውን ፤ጠላው የጠራውን አዘጋጅተው ካህናትን፤የቤተ-ክርስቲያን አገልጋዮችን በየቤታቸው በመጥራት የትንሳኤውን በረከት በአንድ ላይ ያከብራሉ፡፡ይህም ግብረ ሰላም ይባላል፡፡
በሌላ በኩል ግብረ ሰላም ማለት ምዕመናን የክርስቶስን ተዝካር አወጣን
በማለት ስለ ግርፋቱ፤ስለ መንገላታቱ፤ስለመሰቀሉ እና ስለመሞቱ በማሰብ እና በማዘን የክርስቶስ ምሳሌ የሆኑትን ካህናን በመጥራት
ያከብሩታል፡፡በአንጻሩ ካህናት ምዕመናንን አይዟችሁ ክርስቶስ ምንም መከራ ሞት ቢቀበል ሞቶ አልቀረም ከሙታን ተለይቶ ተነስቷል፡፡
በማለት ደስታን ያበስሯቸዋል፤ትንሳኤውን ይሰብኩለቸዋል፤ያረጋጓቸዋል‹‹ሰላም ….እምይእዜሰ፤ይኩን …ፍስሐ ወሰላም ››በማለት ሰላም መታወጁን ይናገራሉ፡፡
በግብረ
ሰላም ጥሪ አድሎ መኖር የለበትም ፡፡አልያ ግብረ ሰላም መሆኑ
ይቀራል፡፡ስለዚህ ግብረ ሰላም ለማድረግ አስቀድሞ