Wednesday, May 29, 2013

ግብረ ሰላም

    
ግብረ ሰላም ማለት ‹‹ ገብረ ሰላመ››መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ሰላምን አደረገ ፤ተጣልተው የነበሩ ሰማያውያን መላዕክት እና ምድራዊያን ደቂቀ አዳም በመስቀሉ ታረቁ ፤ሰላም ወረደ ማለት ነው፡፡ ይሄውም ‹‹የእግዚአብሔር ሙላቱ በእርሱ እንዲኖር በእርሱ በኩልበመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ያሉት ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዷልና› በማለት ቅዱስ ጳውሎስ በቆላ 1፤19-20 ፍንትው አድርጎ ክርስቶስ በመስቀሉ ሰላም እንዳደረገ ገልጾት እናገኛለን፡፡ተድያ ካህናት አባቶች ይህንን ብስራትእና የምስራች ይዘው ከቤተ- እግዚአብሔር ወደ ምዕመናን ቤት‹‹ አዋጅ አዋጅ›› በማለት ይሄዳሉ፡፡ትንሳኤውንም ያበስራሉ፡፡ ይህም ምሰጢር አለው ፡፡ጌታችን እና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ፤ሞቶ፤ወደ መቃብር በወረደብት ጊዜ ሐዋርያት ፍሩኀን ፤ድንጉጻን ነበሩ፡፡በኋላም በ3ኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ በመነሳት ትንሳኤውን በአበሰራቸው ጊዜ ሐሴት አድርገዋል(ዮሐ 20፤20)፡፡በዚህ መሰረት ካህናት የክርስቶስን ትንሳኤ ይዘው ለሐዋርያት  ምሳሌ ለሆኑት ለምዕመናን ክርስቶስ ተነስቷል እያሉ ብስራቱን ይናገራሉ፡፡ካህናት  ለምዕመናን ‹‹ የክርስቶስ ቸርነቱ ብዛቱ፤40 ፆሙ 50 ብሉ ማለቱ ፤ጾም እንዳትውሉ ፤ዘር እንዳትመትሩ›› በማለት ጊዜው የደስታ፤የሐሴት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ምዕመናንም በክርስቶስ ትንሳኤ ደስ በመሰኘት ቀንዱ የዞረዉን፤ጮማው የሰባውን ፤ጠላው የጠራውን አዘጋጅተው ካህናትን፤የቤተ-ክርስቲያን አገልጋዮችን በየቤታቸው በመጥራት የትንሳኤውን በረከት በአንድ ላይ ያከብራሉ፡፡ይህም ግብረ ሰላም ይባላል፡፡  
በሌላ በኩል ግብረ ሰላም ማለት ምዕመናን የክርስቶስን ተዝካር አወጣን በማለት ስለ ግርፋቱ፤ስለ መንገላታቱ፤ስለመሰቀሉ እና ስለመሞቱ በማሰብ እና በማዘን የክርስቶስ ምሳሌ የሆኑትን ካህናን በመጥራት ያከብሩታል፡፡በአንጻሩ ካህናት ምዕመናንን አይዟችሁ ክርስቶስ ምንም መከራ ሞት ቢቀበል ሞቶ አልቀረም ከሙታን ተለይቶ ተነስቷል፡፡ በማለት ደስታን ያበስሯቸዋል፤ትንሳኤውን ይሰብኩለቸዋል፤ያረጋጓቸዋል‹‹ሰላም ….እምይእዜሰ፤ይኩን …ፍስሐ ወሰላም ››በማለት ሰላም መታወጁን ይናገራሉ፡፡
     በግብረ ሰላም ጥሪ አድሎ መኖር የለበትም ፡፡አልያ ግብረ ሰላም መሆኑ ይቀራል፡፡ስለዚህ ግብረ ሰላም ለማድረግ አስቀድሞ

Thursday, May 23, 2013

ፈተና በክርስትና ጉዞ (ክፍል ሁለት)

ምንጭ፦ አትሮንስ - የዲያቆን ኤርምያስ ነቢዩ ገጽ (http://www.ermiasnebiyu.org/)

አንድ ክርስቲያን፤ ክርስቲያን በመሆኑ ብቻ በተለያየ  መልኩ ሊፈተን ይችላል።  ለምሳሌ የግብጽን ክርስቲያኖች ብንመለከት፤ 85% የሚሆነውግብጻዊ እስልምናን ይመርጣል፣የግብጽ መተዳደሪያ የእስላምሻርያ ሕግ እንዲሆን ይፈልጋል፣ የሚሰርቅ ሰው እጆቹ እንዲቆረጡበት ይመኛል፣ ሴቶች እናክርስቲያኖች እንደሁለተኛ ዜጎች ሆነው እንዲኖሩ ያቅዳል። ይህንንም የግብጻውያንን የልብ ትርታበደንብ የተረዱት የእስላም ፓርቲዎች ሴቶች እና ክርስቲያኖች ፕሬዚደንት መሆን እንደማይገባቸው፡እንዲያውም ቁልፍ የሆኑ የሥልጣን ቦታዎችን መያዝ እንደሌለባቸው በመተዳደሪያዎቻቸውአስቀምጠዋል። አሁንም ቢሆን፡ ክርስቲያን ግብጻውያን፡ ፖሊስ መሆን፣ በውትድ ማገልገል፣የእስላም ትምህርት ተቋሞች ውስጥ ገብቶ መማር ወይም ማንኛውም የብሔራዊ የስፖርት ቡድንውስጥ የመሳተፍ መብት የላቸውም። ይህን አሳፋሪ ሁኔታ የዓለም ማሕበረሰብ እንደማያውቅ ሆኖዝም ብሎታል፣ እግዚአብሔር ግን ከቶ አይረሳውም፤ አልረሳቸውምም።
እግዚአብሔርም ለሚወዱት እንደ ሃሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ 8፤28።  ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ያለ ማቋረጥ በትእግስት ልንጠብቀው ይገባል። የጻድቁ የዮሴፍን ታሪክ ብንመለከት ወንድሞቹ በቅንአት መንፈስ ተነሳስተው

Monday, May 20, 2013

ቅዱስ ያሬድ ማን ነዉ?


ኢትየጵያዊዉ ቅዱስ ያሬድ ሚያዝያ 5 ቀን 505 ዓ/ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡እናቱ ታዉክሊያ/ክርስቲና/አባቱ ደግሞ ይስሐቅ/አብድዩ/ይባላሉ፡፡አባቱ የ አክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር፡፡ያሬድ ሰባት ዓመት ሲሆነዉ አባቱ ስለሞቱበት እናቱ ት/ቤት ለማስገባት ወደ አጎቱ መምህር ጌዲዮን ጋር ወሰደችዉ፡፡አባ ጌድዮንም በአክሱም ቤተ ቀጢን(ቤተ ጉባኤ)መምህር ነበሩ፡፡ያሬድ ያኔ በትምህርቱ የሚያሳየዉ ዉጤት ደካማ ስለነበር ከሌሎች ህጻናት ጋር ሊወዳደር አልቻለም፡፡መምህሩ ጌዴዎን ለተግሣጽ ቢቀጡትም መታገስ ተስኖት ተስፋ ቆርጦ ከአክሱም ከተማ ወጥቶ ወደ እናቱ መንደር መደባይ ወለል ተጓዘ፡፡
ህጻን ያሬድ ከዛፍ ስር ተቀምጦ በምን ምክንያት ገጓደኞቹ በታች እንደሆነ ሲያዝን ሲተክዝ ቆየ፡፡ታደሰ አለማየሁ‹‹የቤተ ክርስቲያን ብርሀን ቅዱስ ያሬድ››በሚለዉ መጽሐፉ‹‹አንድ ትል የዛፉን ፍሬ ለመመገብ ፈልጎ ወደላይ እየወጣና እየወደቀ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ ከቆየ በኋላ በሰባተኛዉ ጊዜ ወጥቶ ፍሬዋን ሲመገብ ተመለከተ፡፡ያሬድም የዚህ ትል ተስፋ አለመቁረጥ ትዕግስቱን ጽናቱን ተመልክቶ‹እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ ብዙ ጥረት ካደረኩ እንደዚህ ሊሳካልኝ ይችላል›ብሎ ወደ መምህሩ ለመመለስ ወሰነ ይላል››ያሬድ የ አጎቱ ምክርና ተግሣጽ ለሕይወቱ የሚጠቅም መሆኑን በመረዳቱ ትምህርቱን በትጋት ቢማርና ቢያጠና ያሰበዉ ደረጃ ለመድረስ እንደሚችል በመገንዘብ ወደ መምህሩ ጌዲዮን ጉባኤ ቤት ተመለሰ፡፡መምህሩም ተቀብለዉ አስተማሩት፡፡በአጭር ጊዜ አልገባ ያለዉ ትምህርት ተገልጾለት ትምህርቱን በሚገባ አጠናቀቀ፡፡በኋላም የብሉይና የሐዲስ መምህር ሆኖ በመምህሩ በጌዲዮን ወንበር ተተካ፡፡
የቅዱስ ያሬድ ዜማ እና ዓይነቶቹ
የቅዱስ ያሬድ ዜማ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተገለጸለት ለመሆኑ መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ቅዱስ ያሬድ ዜማዉን ያዘጋጀዉ በሦስት ዓይነት ድምፅ ማለትም በግእዝ፣በዕዝል፣እና በዓራራይ ዜማ ነዉ፡፡እነዚህ የዜማ አይነቶች የአንዱ ድምፅ ከሌላኛዉ ድምፅ ያልተደበላለቀ ወጥ የሆነ ድምፅ አላቸዉ፡፡ዜማዎቹንም በስምንት ምልክቶች ቀምሮታል፡፡የምልክቶች አገልግሎትም በትምህርት ሂደት ጊዜ የጠቋሚነት ሚና በመጫወት ለዜማዉ መጠበቅ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ናቸዉ፡፡
ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀል
ቅዱስ ያሬድ የተነሳዉ ዘጠኙ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ በገቡበት ዘመን ነዉ፡፡በዘጠኙ ቅዱሳን የተተረጎሙት ቅዱሳን መጻሕፍት

እንኳን አደረሳችሁ!!!