የአጋፔ መርሐ ግብር በደ/ም/አ/ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት
ተካሄደ
ሰኔ 3/2005 ዓ/ም
የደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ
ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት አባለትና ስነ ስርዓት ክፍል የአጋፔ መርሐ ግብር ለአባላቱ አዘጋጀ፡፡ሰንበት ት/ቤቱ የአበላትን
የእርስ በእርስ ግንኙነትና መንፈሳዊ ህይወት ለማጠናከር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን የተግባሩ አንድ ክፍል የሆነው ይህ
የአጋፔ ወይም የፍቅር መዓድ መርሐ ግብር በኣባላቱ አማካኝነት እህል ውሃ ከተዘጋጀ በኋላ ለራሴ ልጉረስ ሳይሆን‹‹ ለእህቴና ለወንድሜ
በሚል መንፈስ ሌሎች በዙርያው የሚገኙ አባላትን በማጉረስና በመጉረስ እንዲከናወን ይደረጋል፡፡መርሐግብሩ በወር አንድ ጊዜ እንደ
ሚከናወን የገለጹት የአባላትና ስነስርዓት ክፍል ተጠሪ ወጣት ገ/ሥላሴ
በቤተክርስትያናችን ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ተጠናክሮ መሰራትና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ሆኑን በመግለጽ ፤በምዕመናን፤በሰንበት
ት/ቤት አገልጋዮችና አባላት መካከል ያለውን መንፈሳዊ ግንኙነትና ምክክር ሊያጠንክሩ የሚችሉ ማንኛውም ተግባራት መለመድና መሰራት
እንዳለባቸው አያይዘው ገልጸዋል፡፡በወቅቱ ተሳታፊ የነበሩ አባለትም እንደ ተናገሩት ወደ ሰንበት ት/ቤቱ በአባልነት ከተቀላቀልን
በኋላ እንደ እነዚህ አይነት መርሐ ግብሮችን መካፈል መጀመራችን በመንፈሳዊ ህይወታችን ዙርያ ሊገጥሙ የሚችሉ ማንኛውንም ፈተናዎች
ለማለፍና እህታዊና ወንድማዊ ግንኙነትን ለማጠናከር እጅግ ጠቀሜታ እንደለው በስፋት ገልጸዋል፡፡ በመርሐግብሩ 30 ሴትና 25 ወንዶች
ተካፋይ የሆኑ ሲሆን የደብሩ ቄሰ ገበዝ አባ አክሊሉ በመርሐ ገብሩ ላይ በመገኘት አባታዊ ቡራኬ የሰጡ ሲሆን መርሐ ግብሩ ቤተ-ክርስትያናዊ
መሰረት እንዳለውና ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማለት በጸሎት ካዘጉ በኋላ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሁኗል፡፡
በዲ/ን ዳንኤል ገነቱ
No comments:
Post a Comment