Wednesday, March 13, 2013

ልጆች እንኳን ለአብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ!!!


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
    ልጆች እንደምን ሰነበታችሁ? ደህና ናችሁ! አሜን የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን፡፡ ልጆች እንደሚታወቀው ቤተክርስትያናችን ከምታዛቸው ሰባት የአዋጅ ወይም የትዕዛዝ አጾዋማት መካከል አንዱና ትልቁ የዐብይን (የሁዳዴ) ፆምን ተቀብለናል፡፡ ልጆች ለምን ዐብይ እነደተባለ ታውቃላችሁ? ዐብይ ማለት ስሙ በራሱ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ታላቅ የተባለበት ምክንያት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም በመሆኑ ነው፡፡
     በዐብይ ጾም 8 ሰንበታት (እሁዶች) አሉ፡፡እነዚህ የየራሳቸው ስያሜዎች አሏቸው፡፡
1. ዘወረደ
2. ቅድስት
3. ምኩራብ
4. መፃጉዕ
5. ደብረዘይት
6. ገብርሄር
7. ኒቆዲሞስ
8. ሆሳዕና ናቸው፡፡
እናንተም ይህን ጾም ለመጾም እድሜአችሁ ሰባት አመት ከደረሰ መጾም ይኖርባችኋል፡፡ውድ ልጆች ጾሙን ስንጾም ታዲያ 
       1 ከሰው ጋር አለመጣላት
       2 አለመሳደብ
       3 ለወላጆች መታዘዝ
       4 ታላቅን ማክበር  እና
       5 አስርቱን ትዕዛዛት በሙሉ ማክበር ይገባል እሺ? ጎበዞች
በሉ ልጆች በሚቀጥለው ዕትም እስክንገናኝ ሰላም ሰንብቱ እሺ፡፡

No comments:

Post a Comment