ሰኔ 15/2005 ዓ/ም
የደ/ም/አ/ቅ/ ገብርኤል ሰንበት
ት/ቤት በደብሩ ለሚገኙ የአቋቋም የአብነት ተማሪዎች የአልባሳትና ቁሳቁስ ድገፍ አደረገ፡፡ሰንበት ት/ቤቱ የቤተክርስቲያን አገልግሎት
መሰረትና አንደበት የሆኑትን የአብነት ተማሪዎች ከዚህ በፊት በተለያየ መልኩ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ
በዛሬው ዕለት ያበረከተው ስጦታ መልዕክቱ ከአልባስነት የዘለለ ከቁሳቁስነት ከፍ ያለመሆኑን የሰንበት ት/ቤቱ በጎአድራጎት ክፍል
ሰብሳቢ ወጣት ኃይለ ገብርኤል የገለጹ ሲሆን በቀጣይ ጊዜ በአብነት ትምህርት ቤቶች ዙርያ ለሚሰሩ ሰፋፊ የጤናና ሌሎች የመሰረተዊ
ፍላጎት ፕሮጀክቶችን በተደራጀ መልኩ ለማስጀመር የመግቢያ መርሐ-ግብር መሆኑን ገልጸዋል፡፡በመርሐ ግብሩ የተለያዩ ምግባረ-ሰናይን
የተመለከቱ መርሐ-ግብሮች የቀረቡ ሲሆን ከተለያየ ቦታ የተሰበሰቡ አልባሳትና ቁሳቁሶች ለ40 የአብነት ተማሪዎች ከተበረከቱ በኋላ
መርሐ-ግበሩ በጸሎት ተዘግቶ ተጠናቋል፡፡
ዮሐንስ ተረፈ
No comments:
Post a Comment