ዜና አቡን ቤት ቅ/ገብርኤል ሰ/ት/ቤት
የደ/ም/አ/ቅ/ገብርኤል
ሰ/ት/ቤት ‹‹ትውልዱን ወደ ሰ/ት/ቤት ማቅረብ ››በሚል መሪ
ቃል በዓይነቱ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ መርሐ ግብር የየካቲት 16/06/05እና17/06/05ዓ/ም ለ2 ተከታታይ ቀናት አካሔደ ፡፡በዕለቱም
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ተጋብዘው ከጉባኤው ዓላማ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስብከቶችን የሰጡ ሲሆን የተለያዩ ያሬዳዊ ዜማዎች፤ጭውውቶች
፤መነባንቦችም ቀርበዋል ፡፡በጉባኤውም እጅግ በርካታ ምዕመናን በመገኘት የመንፈሳዊ ግብዣ ተቋዳሽ ከመሆናቸውም በተጨማሪ በሰ/ት/ቤቱ
አባል ሆኖ በመታቀፍ የሚጠበቅባቸውን ክርስቲያናዊ ግዴታ ለመወጣትም ቃል ገብተዋል፡፡ የአቡን ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት በሰንበት
ት/ቤቱ አባል ሁነው ለማገልገል ቃል ለገቡት የጉባኤው ታደሚዎች በሌላኛው ቀን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐ ግብር በማዘጋጀት ሰንበት
ት/ቤት ለነገይቷ ቤተክርስቲያን ህልውና ወሳኝና እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ በሰንበት ት/ቤቱ አባልና አገልጋይ ሆኖ ለመቀጠልም መንፈሳዊ
ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ በስፋት ተብራርቶላቸዋል ፡፡በእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐ ግብሩ የእግር አጠባ ፤የተለያዩ ትምህርታዊ
ስነ ጽሑፎችና ያሬዳዊ ዜማዎችም ቀርበው እንደነበር ለማውቅ ተችሏል ፡፡፤
በጎንደር ከተማ የሚገኙ የተለያዩ አብያተ ክርስትያናት ዲያቆናት አገልጋዮች
በሐዋርያዉ ፊሊጶስ ስም የጽዋ ማህበር በቅርቡ መሰረቱ ፡፡የጽዋ ማህበሩ በዋነኝነት መመስረት ያስፈለገበት ምክንያት ዲያቆናት እርስ
በእርስ እንዲተዋወቁ ፤በጎ ልምዳቸዉን እንዲለዋወጡ፤በቤ/ ክ ዙሪያ
በይበልጥም ከዲቁና ተግባር ጋር ተያይዞ ስለሚፈጸሙ አገልግሎቶች በቂ
ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ብሎም ከምንፍቅና ተግባር ተቆጥበው ቤተ ክርስቲያናቸዉን ከቀሳጥያን በትጋት እንዲጠጠብቁ፤ነገም ለቅስናና ለምንኩስና
በመብቃት በትህትና ቅ/ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ፤ ለማድረግ ታስቦ ነዉ፡፡ይህ የማህበሩ ዓላማ ለዲያቆናቱ በደንብ ተብራረቶ
የተገለጸ ሲሆን የመንበረ መንግስት መድኃኔዓም አስተዳዳሪ እና የአራቱ ጉባኤ ምስክር የሆኑት ሊቀ ሊቃዉንት ዕዝራ ሐዲስ በዲያቆናቱ
የጽዋ ማህበር በመገኝት ስለ ሚስጥረ ክህነትና በጎ አገልግሎቱ በስፋት አስተምረዋል፡፡አያይዘዉም‹‹ዲያቆናት በብዙ መልኩ ፊት አዉራሪ
መሆን ሲገባቸዉ በብዙ መልኩ ተቀዛቅዘዉ››መቆየታቸዉን ጠቅሰዉ ግን እንደዚህ የተደራጀ የጽዋ ማህበር መመስረቱ እንዳስደሰታቸዉ ገልጸዋል፡፡
ይኼ የጽዋ ማህበርም ታይቶ በሚጠፋ ባአሽዋ ላይ የተመሰረተ ቤት እንዳይሆን በጥብቅ አሳስበዋል፡፤ ማኅበረ ፊሊጶስ አባላቱን ለማብዛት
ከመቸዉም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ የጽዋ ማህበሩ አስተባባሪዎች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡
የደብረ ምህረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት በሰሜን ጎንደር
ዞን ማረሚያ ቤት የተጠናከረ የወንጌል አገልግሎት መስጠት ጀመረ ፡፡በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ ክርስቲያን ታራሚዎች ከዚህ ቀደም የተጠናከረ
መንፈሳዊ ት/ት ማግኘት አለመቻላቸውን ጠቅሰው ሰንበት ት/ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት በቅዱስ መጽሐፍ እንደታዘዘው ወንጌል የተራብነውን
እኛን እዚህ ድረስ በመምጣት ማገልገሉ ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል ፡፡ሰንበት ት/ቤቱ በማረሚያ ቤቱ በዕለተ ዕሁድ ለ 2ሰዓት የሚቆይ ሰብከት ፤ያሬዳዊ መዝሙር ፤እንዲሁም አጽናኝ
የሆኑ ስነ ጽሑፎች የሚያቀርቡ ሲሆን በሳምንት አንድ ቀን በሚያካሂደው በዚህ መንፈሳዊ ዝግጅት ተቋዳሽ የሚሆኑ የህግ ታራሚዎች ይበል
የሚያሰኝ የባህርይ ለውጥ ማምጣት እንደቻሉ ለመረዳት ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment