Friday, July 5, 2013

የደ/ም/አ/ቅ/ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት ለአብነት ተማሪዎች የአልባሳትና ቁሳቁስ ድገፍ አደረገ፡፡


ሰኔ 15/2005 ዓ/ም


    የደ/ም/አ/ቅ/ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት በደብሩ ለሚገኙ የአቋቋም የአብነት ተማሪዎች የአልባሳትና ቁሳቁስ ድገፍ አደረገ፡፡ሰንበት ት/ቤቱ የቤተክርስቲያን አገልግሎት መሰረትና አንደበት የሆኑትን የአብነት ተማሪዎች ከዚህ በፊት በተለያየ መልኩ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ በዛሬው ዕለት ያበረከተው ስጦታ መልዕክቱ ከአልባስነት የዘለለ ከቁሳቁስነት ከፍ ያለመሆኑን የሰንበት ት/ቤቱ በጎአድራጎት ክፍል ሰብሳቢ ወጣት ኃይለ ገብርኤል የገለጹ ሲሆን በቀጣይ ጊዜ በአብነት ትምህርት ቤቶች ዙርያ ለሚሰሩ ሰፋፊ የጤናና ሌሎች የመሰረተዊ ፍላጎት ፕሮጀክቶችን በተደራጀ መልኩ ለማስጀመር የመግቢያ መርሐ-ግብር መሆኑን ገልጸዋል፡፡በመርሐ ግብሩ የተለያዩ ምግባረ-ሰናይን የተመለከቱ መርሐ-ግብሮች የቀረቡ ሲሆን ከተለያየ ቦታ የተሰበሰቡ አልባሳትና ቁሳቁሶች ለ40 የአብነት ተማሪዎች ከተበረከቱ በኋላ መርሐ-ግበሩ በጸሎት ተዘግቶ ተጠናቋል፡፡

ዮሐንስ ተረፈ

No comments:

Post a Comment